Skip to main content

KingCounty.gov is an official government website.

Official government websites use .gov
Website addresses ending in .gov belong to official government organizations in the United States.
Secure .gov websites use HTTPS
A lock or https:// means you've safely connected to the .gov website. Only share sensitive information on official, secure websites.

የበላይ ፍርድ ቤት የጸሃፊ ጽሕፈት ቤት አጠቃላይ እይታ

የኪንግ ካውንቲ የዳኝነት አስተዳደር ክፈል (DJA)፣ በተለምዶ አጠራር የከፍተኛ ፍርድ ቤት ጸሃፊ ጽህፈት ቤት በመባል የሚታወቀው፣ ለኪንግ ካውንቲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደ መዝገብ ጠባቂና የደንበኞች አገልግሎት የሚያቀርብ ሆኖ ያገለግላል፡፡

ከ 1854 ጀምሮ የጸሐፊው ጽህፈት ቤት ይፋዊ የላቁ የፍርድ ቤት ጉዳዮች መዝገቦችን የመጠበቅና የማስተዳደር ኃላፊነት አለበት፡፡ የጉዳይ መዝገቦች አልፎ አልፎ በሚኖሩ ልዩ ሁኔታዎች፣ የህዝብ መዝገቦችና ለአጠቃላይ እይታ ይገኛሉ፡፡ ለሕዝብ ቁጥጥር ስር ያልሆኑ መዝገቦች በፍርድ ቤት ትእዛዝ የታሸጉ፣ በፍርድ ቤት ደንብ ወይም በሕግ ጥበቃ የሚደረግላቸው ናቸው፡፡

የጸሐፊው ቢሮም እንዲሁ ደረሰኝ፣ ወጪንና የሁሉም ክፍያዎች፣ ቅጣቶች የሂሳብ አያያዝና በከፍተኛ የፍርድ ቤት ጉዳዮች ላይ የተደረጉ ክፍያዎች ያስተዳድራል፡፡ በጸሐፊ የህግ የገንዘብ ግዴታዎች ስብስብ ፕሮግራም የተሰበሰቡ የወንጀልና የወጣት ወንጀለኛ ጉዳዮች ላይ ፍርድ ቤቱ የታዘዘ ክፍያዎች ተካትተዋል፡፡

ሌሎች የልዩ ባለሙያተኛ የጸሃፊ የጽሕፈት ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ፕሮግራሞች፡ በጸሐፊው ጥበቃ ትእዛዝ ጽሕፈት ቤት አማካይነት ሕዝቡን መርዳት፣ በኑዛዜ ሜዣ በኩል ደህንነቱ የተጠበቀ የኑዛዜ መያዣ ማቅረብ፣ የፍርድ ቤት መዝገቦችንና የሰነድ ቅጂ ጥያቄዎችን በመስመር ላይና በአካል ማግኘት እንዲቻል ማመቻቸት እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ የዳኝነት ስራ ቅጂዎችን በኤሌክትሮኒክ መንገድ መሙላትና እንዲቀርብ ማስቻል፡፡ በተጨማሪነትም በእያንዳንዱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ ሁሉ ጸሃፊው መገኘት ይጠበቅበታል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን ፕሮግራሞችን የጸሐፊው ሰራተኞች ያስተዳድራሉ፡ የአዋቂዎች እጽን የሚመለከት ፍርድ ቤት (Adult Drug Diversion Court)፣ የቅድመ ዳኝነት ፕሮግራም ሲሆን ይህም የተዋቀረ የፍርድ ቤት ቁጥጥርና ከዋናው የአደንዛዥ እጽ አጠቃቀም ችግር ጋር በተያያዙ ከባድ ወንጀሎች ተከሰው ብቁ ግለሰቦች አገልግሎቶችን የሚሰጥ ነው፤ እንዲሁም ደግሞ የ KC የጽሁፍ ስርአት በኤሌክትሮኒክ መንገድ ሰነድ ማቅረቢያ፣ አስተዳደር፣ ማስቀመጥ፣ ፈልጎ ማውጣትና ለፍርድ ቤት፣ ለጸሃፊ ቢሮ ሰራተኞች፣ ለህዝብና ለህግ፣ ለደህንነትና ለፍትህ አጋር ኤጀንሲዎች የሚሰጥ የቴክኖሎጂ ስርአት ነው፡፡

የጸሐፊው ጽህፈት ቤት ቦታዎች፡

King County Courthouse
516 Third Avenue, Rm E-609 
Seattle, WA 98104

Maleng Regional Justice Center 
401 Fourth Avenue N, Rm 2C
Kent, WA 98032

Clark Children & Family Justice Center
1211 East Alder, Rm3015
Seattle, WA 98122

የጸሃፊ ጽሕፈት ቤት ሰአት፡ ከሰኞ – አርብ 9:00 ኤኤም -12:15 ፒኤም እና 1:15 ፒኤም – 4:30 ፒኤም (ውስን አገልግሎቶች 12:15 – 1:15 ፒኤም)፣ በሕግ ከተደነገጉ በአላት በስተቀር፡ kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/court-calendars-locations-operations/locations-hours

የጸሐፊ ደንበኛ አገልግሎት፡ ሰራተኞች ደንበኞችን ለመርዳት በማንኛውም የጽህፈት ቤቱ መቀበያ በስልክ (206-296-9300) ወይም በኢሜል፡ DJA.CustomerServiceEmail@KingCounty.gov ይገኛሉ፡፡ ስለ ጸሐፊው ኤሌክትሮኒክ መተግበሪያዎች ጥያቄዎች የኢአገልግሎት እገዛ ዴስክን ያግኙ፡ 206-477-3000 ወይም eServices@kingcounty.gov ፡፡

የጉዳዩ ቁጥር መፈለጊያ፡ የጉዳይ ቁጥሩ የማይታወቅ ከሆነ የፀሐፊው መዝገቦች ማግኛ ፖርታል (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡) የመስመር ላይ የጉዳይ ቁጥርና የሰው መፈለጊያ ያቀርባል፡፡ 

የፍርድ ቤት ቅጾች፡ ቅጾችና ሰነዶች በመስመር ላይ ይገኛሉ፡ kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/court-forms-document-filing/forms ፡፡ (የተገናኘው ገጽ አልተተረጎመም፡፡)

የክፍያ መርሃ ግብር፡ የጸሃፊው ጽህፈት ቤት ክፍያዎች በሕግ ወይም በፍርድ ቤት የተደነገጉ ሲሆኑ እነዚህም አስቀድሞ መከፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ስለክፍያ ክፍያዎች ወይም ስለሚኖሩ ወጪዎች ቅናሽ ለማወቅ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ www.kingcounty.gov/courts/clerk/fees ፡፡

ኢ-ፋይሊንግ (የተገናኙ ገጾች አልተተረጎሙም፡፡.): አብዛኛዎቹ ሰነዶችን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዮች በኤሌክትሮኒክ መንገድ መመዝገብ ለጠበቆች ግዴታ ነው (KCLGR 30ይመልከቱ)፡፡ ስለ ኢ-ፋይሊንግ የበለጠ ለማወቅ የሚከተለውን ይጎብኙ፡ kingcounty.gov/en/dept/dja/courts-jails-legal-system/court-forms-document-filing/filing/e-filing ፡፡ 

ይህን ትርጉም በተመለከተ አስተያየት ስለሰጡን እናመሰግናለን።