የመርዛማ ውጋጅ መረጃ እና አገልግሎቶች
የሚኖሩት ወይም የሚሰሩት ኪንግ ካውንቲ ውስጥ ከሆነ፣ ራስዎን እና አካባቢዎን ከመርዛማ ውጋጅ እንዲከላከሉ ለመርዳት ምቹ የሆኑ አደገኛ ቆሻሻ ማስወገጃ ዘዴዎችን እና መረጃዎችን እናቀርብልዎታለን።
ስለ እኛ
ሃዛርደስ ዌስት ማኔጅመንት ፕሮግራም (Hazardous Waste Management Program) በአደገኛ ምርቶች አመራረት፣ አጠቃቀም፣ አቀማመጥ እና አወጋገድ የተነሳ የሚፈጠሩ ስጋቶችን በመቀነስ በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የማህበረሰብ ጤናና የአካባቢ ንጽህናን ይጠብቃል እንዲሁም እንዲሻሻል ያደርጋል። የሲያትል ከተማን፣ 37 ሌሎች ከተሞችን፣ ሁለት ጎሳዎችን እና ያልተካተቱ ቦታዎችን ጨምሮ ለሁሉም የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች አገልግሎት የምንሰጥ ክልላዊ ሸሪክ ነን።የተለመዱ መርዛማ ምርቶች
ያልተጠቀምንባቸው፣ ያረጁ ወይም አስፈላጊ ያልሆኑ መርዛማ ምርቶችን ማስቀመጥ አደገኛ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ምርቶች ከቆሻሻ ጋር ከተጣሉ ወይም ከፍሳሽ ማስተላለፊያ ጋር ከተቀላቀሉ በሰዎችም ሆነ አካባቢ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። መርዛማ ምርቶች መሆን አለመሆናቸውን የምርቶቹ ተለጣፊ ምልክት ላይ ማንበብ ይችላሉ። እነዚህ መርዛማ ምርቶች ተለጣፊ ምልክት አላቸው ይህም danger (አደገኛ) ፣ poison (መርዝ) ፣ warning (ማስጠንቀቂያ) ፣ ወይም caution (ጥንቃቄ) የሚሉ ቃላቶችን ይይዛል።
ደህንነቱ የተጠበቀ አወጋገድ 3 ደረጃዎች
-
እቃዎቹን ይሰብስቡ፡
ልጥፉ የሚከተሉት ቃላት ካሉት DANGER (አደገኛ) ፣ POISON (መርዝ) ፣ WARNING (ማስጠንቀቂያ) ፣ ወይም CAUTION (ጥንቃቄ) ፣ ይህ መርዛማ ውጋጅ ነው።
የምንቀበላቸውን የእቃዎች ዝርዝር ይመልከቱ። [Link to what to bring flyer] -
ለማስወገድ የሚደረጉ ዝግጅቶች፡፡
የሚወገዱትን እቃዎች በራሳቸው መያዣ ውስጥ ያስቀምጡ፣ ምርቶቹ ምልክት ካልተደረገባቸው ምልክት ያድርጉባቸው እንዲሁም ምርቶቹ እንዳይንጠባጠቡ ወይም እንዳይፈሱ በጥንቃቄ ይዝጉ። ምርቶቹን ከተሸከርካሪዎ የተሳፋሪዎች መቀመጫ አርቀው ያስቀምጡ። -
ማስወገጃ ቦታ፡-
የሚወገዱትን እቃዎች ወደ ማስወገጃ ቦታ ያምጡ። አገልግሎቱ በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነት የሚሸፈን በመሆኑ ምንም ክፍያ አይከፍሉም።
በአቅራቢያዎ የሚገኝ የማስወገጃ ቦታ ይፈልጉ።
Location | Address | Hours |
---|---|---|
North Seattle |
እሁድ – ማክሰኞ |
|
South Seattle |
ሐሙስ – ቅዳሜ |
|
Factoria |
ማክሰኞ – ዓርብ፥ ቅዳሜ እና እሁድ |
|
Auburn |
ቅዳሜ - እሁድ |
Wastemobile – ተንቀሳቃሽ የመርዛማ ውጋጅ መሰብሰቢያ አገልግሎት
ይህ ነጻ የቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ለኪንግ ካውንቲ ነዋሪ ማህበረሰቦችን እና አነስተኛ የንግድ ስራዎችን የቤት ውስጥ መርዛማ ውጋጆቻቸውን የሚወስዱበት ምቹ ቦታ ለመምረጥ ጉብኝቶችን ያደርጋል።
የ ዌስትሞባይል ተዘዋዋሪ የቤተሰብ መርዛማ ውጋጅ ማንሻ አገልግሎት፣ ከእርስዎ አጠገብ የሚገኙ አካባቢዎችን የሚጎበኙበትን ጊዜ ይወቁ። [link WMB schedule]
የቤት ለቤት መሰብሰብ ፕሮግራም
እድሜዎ ከ65 አመት በላይ ነው ወይም የአካል ጉዳተኛ ነዎት? ተሽከርካሪ ከሌለዎት እና ከዚህ ውጪ የመርዛማ ውጋጅ መሰብሰብያ ጣቢያ መሄድ የማይችሉ ከሆነ፣ ወደ እኛ በመደወል ከቤትዎ ቆሻሻ የማንሳት ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። የቤት ለቤት መሰብሰብ ፕሮግራም በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነት ይከፈላል፤ ስለሆነም ቆሻሻዎን ለማንሳት ክፍያ አይጠየቁም።በኪንግ ካውንቲ ውስጥ የንግድ ድርጅት አለዎት?
የንግድ ባለቤት እንደመሆንዎ፣ አደጋን ሊያስከትል የሚችል ቆሻሻዎን በሰራተኞችዎ፣ ማህበረሰቡ ወይም አካባቢዎ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በአግባቡ ማስወገድ የእርስዎ ኃላፊነት ነው። ብቁ ለሆኑ የንግድ ስራዎች መርዛማ ውጋጃቸውን በነጻ እንዲያስወግዱ እገዛ ማድረግ እንችላለን። በተጨማሪም በቦታው በመገኘት የማማከር አገልግሎቶች፣ አካባቢን መሰረት ያደረጉ ምክሮች እና የማሻሻያ ተመላሽ ጥሬ ገንዘብ መስጠት እንችላለን። እነዚህ አገልግሎቶች በሙሉ ክፍያቸው በእርስዎ የአገልግሎት ክፍያ አማካኝነትስለሚሸፈን ለአገልግሎቶቹ ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይጠየቁም።