Skip to main content

በኪንግ ካውንቲ ውስጥ በሚኖሩ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ አባል በሆኑ ልጆች፣ በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች እና አዋቂዎች መካከል የተከሰተው የሺጋ መርዝ-የሚያመነጨው ኢ. ኮሊ (STEC) O157:H7 ኢንፌክሽኖች፣ ምንጩ አልታወቀም.

በጨረፍታ
የተረጋገጡ ክስተቶች 8
ያልተረጋገጡ ነገር ግን ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶች 0
የዕድሜ ክልል ከ11 ወር እስከ 35 ዓመት የሆኑ (5 ክስተቶች ዕድሜአቸው ከ15 ዓመት በታች በሆኑ ልጆች ላይ ተገኝቷል)
ሪፖርት የተደረገበት ቀን ዲሴምበር/ታህሳስ 31/2021 - ኦገስት/ነሃሴ 18/2022
በበሽታው ምክንያት ሆስፒታል የተኙ 6

በዲሴምበር 5፣ 2022 ተሻሽሏል


ማጠቃለያ

የህዝብ ጤና ኪንግ ካውንቲ ውስጥ የሺጋ መርዝ-በሚያመነጨው ኢ.ኮሊ [E. coli] (ወይም [STEC] በመባል በሚታወቀው) አዲስ ወረርሽኝ በተያዙ ስምንት ግለሰቦች ላይ ምርመራ አድርጏል። ከአንዱ ክስተት በስተቀር ሁሉም ክስተቶች ከጁን 26፣ 2022 ጀምሮ ሪፖርት ተደርገዋል። ሁሉም ክስተቶች የተገኙት በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰቦች ላይ ነው።

አብዛኛዎቹ የታመሙ ሰዎች በተጋላጭነት ጊዜያቸው ፍየል እና የተፈጨ የበሬ ሥጋን ጨምሮ በርካታ የስጋ ዓይነቶችን እንደበሉ ተናግረዋል ። የጄኔቲክ አሻራ ውጤቶቹ (ሙሉ የጂኖም ቅደም ተከተል [(WGS)]) እንደሚያመለክቱት ሁሉም ክስተቶች የታመሙበት ኢንፌክሽን ከአንድ አይነት ዘር እንደመጣ፣ ማለትም የጋራ የኢንፌክሽን ምንጭ እንዳላቸው ያሳያል።

ሕመሞች

ሁሉም ግለሰቦች እንደ ተቅማጥ (ብዙውን ጊዜ ደም የቀላቀለ)፣ ሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ እና እንደ ትውከት ያሉ ከ [STEC] ጋር የተያያዙ የሕመም ምልክቶች ነበራቸው። ከአንዱ ግለሰብ በስተቀር ሌሎቹ ግለሰቦች ህመሙ የጀመራቸው ከጁን 20 - ኦገስት 17፣ 2022 ባሉት ጊዜያት ውስጥ ነው ። አንድ ተጨማሪ ግለሰብ ህመሙ ዲሴምበር 2021 ላይ እንደጀመረው በ [WGS] መለየት ተችሏል። ሶስት ልጆች ሄሞሊቲክ ዩሬሚክ ሲንድሮም [(HUS)] የሚባል የኩላሊት በሽታ አጋጥሟቸዋል። ሁሉም ግለሰቦች ከበሽታው አገግመዋል።

የህዝብ ጤና እርምጃዎች

የህዝብ ጤና አስተዳደር ማናቸውንም የተለመዱ ተጋላጭነቶችን ለመለየት እና ተጨማሪ ስርጭቶችን ለመከላከል የሚረዳ መመሪያ ለመስጠት በSTEC በሽታ ከተያዙ ግለሰቦች ወይም በበሽታው ከተያዙ ልጆች ወላጆች/አሳዳጊዎች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። ተጨማሪ ምርመራን ለመጨረስ፣ በሌሎች አውራጃዎች ውስጥ ተዛማጅ ጉዳዮችን ለመለየት እና የጋራ ምርቶችን መከታተል ለመጀመር ከዋሽንግተን ስቴት የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት ጋር ሠርተናል። እንዲሁም ስለዚህ ወረርሽኝ መረጃ እና መመሪያ ለመለዋወጥ እና ተጨማሪ ኢንፌክሽኖችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በቅርበት ሰርተናል።

የእነዚህ ኢንፌክሽኖች ምንጭ ምርመራ ተጠናቅቋል። እንደ የምርመራው አካል፣ የህብረተሰብ ጤና ሰራተኞች በ [STEC] የታመሙ ግለሰቦች በኢንፌክሽኑ ከመያዛቸው በፊት ምግብ ገዝተናል ብለው ካሰቡባቸው በርካታ የምግብ ተቋማቶች ላይ በርካት ጥናቶችን አድርገዋል። ተቋማቶቹን በሚጎበኙበት ጊዜ፣ የህብረተሰብ ጤና ሰራተኞች የ [E. coli] ስርጭትን እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ለተቋማቶቹ ትምህርት ሰጥተዋል። በተጨማሪም ለተቋማቶቹ አስተዳደር የምግብ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ ንጹህ እንዲያደርጉና ፀረ-ህዋስ መዳኒትን ተጠቅመው እንዲያጸዱ መመሪያ ሰጥተዋቸዋል።

የህዝብ ጤና መልእክት

እንደ የተፈጨ የበሬ ሥጋ፣ የፍየል እና የበግ ጥሬ ስጋዎች አንዳንድ ጊዜ እንደ STEC ባሉ ጀርሞች ሊሞሉ ይችላሉ፣ በዚህም የተነሳ ቀደም ባሉት ጊዜያት ላይ ከወረርሽኞች ጋር ተያይዘው ተገኝተዋል። በSTEC እንዳይታመሙ እነዚህን አራት የምግብ ደህንነት ደረጃ ምክሮች ይከተሉ።

  • ንፅህና፡ እጅዎን፣ የምግብ እቃዎችን እና የማብሰያ ቦታን ቶሎ ቶሎ ያፅዱ። ከመብላትዎ፣ ከመቁረጥዎ ወይም ከመላጥዎ በፊት ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በሚፈስ ውሃ ስር ለተወሰነ ጊዜ ያለቅልቁ ።
  • መለያየት፡ በእሳት ላይ መብሰል የሌለባቸውን ምግቦች ከጥሬ ስጋ፣ ከዶሮ ስጋ እና ከባሕር እንስሳት የተዘጋጀ ምግብ ለምሳሌ እንደ አሳ ስጋ ካሉ ነገሮች ነጥለው ያስቀምጡ።
  • ምግብ አበሳሰል፡ ምግብዎ ላይ ያሉትን ጀርሞች ለመግደል የሚችል በቂ በሆነ የሙቀት መጠን ማብሰልዎን ለማረጋገጥ የምግብ ቴርሞሜትር ይጠቀሙ።
  • ማቀዝቀዝ፡ የሚበላሹ ምግቦችን (በቶሎ ሊበላሹ የሚችሉ ምግቦችን) በ2 ሰአታት ውስጥ ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስገባት። ምግቡ ከ 90 ዲግሪ ፋራናይት በላይ ለሆነ የሙቀት መጠን ከተጋለጠ (ለምሳሌ የሞቀ መኪና ውስጥ ወይም የሚሞቅ ቦታ ላይ ከነበረ) በ 1 ሰዓት ውስጥ ማቀዝቀዣ ውስጥ ይክተቱት። በረዶ የያዘን ምግብ ውጭ በሚያበስሉበት ቦታ ላይ ሳይሆን በማቀዝቀዣ ፍሪጅ ውስጥ ያቅልጡት።

እርስዎ ወይም ልጅዎ ከፍተኛ ህመም ወይም ደም የቀላቀለ ተቅማጥ ከያዞት፣ ተቅማጡ ከ3 ቀናት በላይ ከቆየ ወይም ከተቅማጡ ጋር ከፍተኛ ትኩሳት ካሎት ወይም ሽንትዎት ከቀነሰ፣ STEC እንዳለቦት ለማወቅ በአቅራቢዎት ያለ የጤና እንክብካቤ ያነጋግሩ።

ይህ በሽታ ለከባድ ወይም ለሕይወት አስጊ ለሆኑ ኢንፌክሽኖች ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች እንዳይተላለፍ ማረጋገጥ እንፈልጋለን። የበሽታው ምልክት ያለባቸው ልጆች ወደ ህፃናት መዋያ ወይም ቅድመ ትምህርት ቤት መሔድ የለባቸውም። በምግብ አገልግሎት፣ በጤና እንክብካቤ ወይም በህጻናት እንክብካቤ መስጫ ቦታዎች ላይ የሚሰሩ ሌሎች የታመሙ ግለሰቦች ወደ ሥራ መሄድ የለባቸውም። ወደ ሥራ፣ የሕጻናት እንክብካቤ ወይም ቅድመ ትምህርት ቤት ከመመለሳችሁ በፊት በሽታውን ለሌሎች ግለሰቦች አለማስተላለፎትን ለማረጋገጥ የሕዝብ ጤና ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርጉ ይረዳዎታል።

የላብራቶሪ ምርመራ

ከሁሉም ክስተቶች በተወሰደ ናሙና አማካኝነት የ ኢ. ኮላይ O157:H7 ኢንፌክሽን እንደተያዙ የሚያረጋግጥ ምርመራ አድርገዋል። በዋሽንግተን ስቴት የህዝብ ጤና ላቦራቶሪ ውስጥ በተደረገው የጄኔቲክ አሻራ (ሙሉ ጂኖም ቅደም ተከተል ወይም WGS) ምርመራ መሰረት ሁሉም ክስተቶች ተመሳሳይ የSTEC ኢንፌክሽን ናቸው።

expand_less