ለልጆች ጥሩ ጅማሬ የሚሆን የጤና ቃለ መጠይቅ
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወይም ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ያሏቸውን የኪንግ ካውንቲ ቤተሠቦች ያካተተ ጥናት
ጥሩ ጅማሬ ለልጆቸ ተብሎ የሚታወቀው በመላው ኪንግ ካውንቲ በሚገኙ ማኅበረሰቦች ውስጥ በተለይ በልጆች ላይ ኢንቨስትመንት ማድረጉን ቀጥሏል ። ለልጆች ጥሩ ጅማሬ የሚሆን የጤና ጥናት ስለልጆቻችን ጥንካሬ፣ ከፍተኛፍላጎት እንዲሁም በማኅበረሰባችን ውስጥ ያሉ ለውጦችን እንድንረዳ ይረዳናል ።
ወላጅ መሆን ከባድና ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ነው። በወላጅነት ውስጥ ያለ ተመክሮን መማማር፣ ስለ ልጆች ጤንነት፣ የቤተሰብ ጥንካሬእና የማህበረሰብ ድጋፍ ያላችሁን ተሞክሮ መማር በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ያሉ ልጆች ሁሉ ደስተኛ እና ጤናማ እንዲሆኑ ያግዛል የሚል ተስፋ አለን::
ጥሩ ጅማሬ ለልጆች የተባለው ከዩኒቨርስቲ ኦፍ ዋሽንግተን የማኅበራዊ ሥራ ጥናት ምርምር ክፍል ጋር በመሆን የልጆችን ጤንነትን አስመልክቶ ጥናት በማድረግ ላይ ይገኛል ። ተሳታፊዎቹ በደብዳቤ ወይም በስልክ አማካኝነት የሚገናኙ ሲሆን ስለ ልጆች የሚደረገው የጤና ጥናት ደግሞ በኢንተርኔት / ኦንላይን ወይም በስልክ ሊጠናቀቅ ይችላል።
ልጄ ለዚህ ጥናት በአጋጣሚ የሚመረጠው እንዴት ነው?
ቤተሰባችሁ ደብዳቤ በፖስታ ከደረሳቸው ልጃችሁ በአጋጣሚ እንዲሳተፍ ተመርጧል/ለች ማለት ነው።
- የልጃችሁ ስም እና የወላጅ/አሳዳጊ አድራሻ መረጃ በህዝብ ጤና – ሲያትልና ኪንግ ካውንቲ ከዋሽንግተን ስቴት የጤና መስሪያ ቤት እና ኪንግ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ጋር በመተባበር ጥራቱን በጠበቀና በአስተማማኝ ሁኔታ ይሰበስባሉ።
- በአጋጣሚ የአመራረጥ ስልት አማካኝነት ሲመረጥ፣ ውጤቱ የሁሉንም የኪንግ ካውንቲ ልጆች ያላቸውን ቤተሰቦች አስተያየትና ተሞክሮ የሚያንፀባርቅበት የተሻለ ዕድል አለ።
ጥናቱ መረጃዎቼን አስተማማኝና ሚስጥራዊ አድርጐ የሚጠብቀው እንዴት ነው?
- መልሳችሁ ሁሉ ምሥጢር ነው ። ምላሾችን ማየት የሚችሉት ምስጢራዊ መረጃዎችን ይዘው ለመስራት ፈቃድ ያላቸው የሰለጠኑ ሰራተኞች ብቻ ሲሆኑ መረጃዎቹ በሙሉ አስተማማኝ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በጥንቃቄ ይቀመጣሉ።
- ምላሾችን ሚስጥራዊ ለማድረግ የልጆች ስም ይወገዳል እና የአጠቃላይ እይታው ውጤት ብቻ በይፋ ይጋራል። ማንም ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ተለይቶ ሊታወቅ አይችልም። እና መረጃው የሚሰበሰበው ጥሩ ጀማሬ ለልጆች የሚሆኑ መገሻዎችን ለማሳወቅ ብቻ ነው::
- የእርስዎ መረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት ለማቅረብ አስተማማኝ ነው:: ማንኛውም ኢንፎርሜሽን ወይም መረጃ የሚሰበሰበው ጥብቅ የደህንነት እና ኢንክሪፕሽን መስፈርቶችን በጠበቀ ደረጃ ብቻ ነው::
- ከዚህ በታች ያሉትን የርሶንም ሆነ የልጅ ሆን በፍፁም አንጠይቅም :
- የሶሻል ሴኪውሪቲ ቁጥር
- የክሬዲት ካርድ ኢንፎርሜሽን
- የባንክ አካውንት ኢንፎርሜሽን
- ገንዘብ ውይም እርዳታ
ለበለጠ መረጃ ከዚ በታች ያለውን መረጃ በመጠቀም ጥያቄዎን ማቅረብ ይቻላሉ
Tewodros Ayele